Mission Statement The Ethiopian Community Los Angeles, ECLA, is an inclusive, nonpolitical, and nonreligious civic organization aiming to address the social, economic, and educational needs of Ethiopian immigrants, and others in similar situations, residing in the Greater Los Angeles area of Southern California. ECLA is committed to promote the history and the cultural heritage of Ethiopia at large. |
Welcome to Ethiopian Community Los Angeles
Our hearts goes out everyone that has been devastated by the recent wildfires. Mutual Aid LA Network has put together a list of resources that is being updated in real-time for those in need throughout LA County. We've pulled a few resources from their list and highlighted below for ease. You can also find additional information and resources HERE. Take care and stay safe LA ❤️ Mental Health Resources SAMHSA Disaster Distress Helpline 800-985-5990 CalHOPE Warmline 833-317-4673 Crisis Text Line by texting LA to 741741 iPrevail app connects to 24/7 on-demand support Mental Health and Stress After An Emergency (LACDMH / DPH) Additional DMH Disaster Mental Health Resource PBS: How to Talk to Kids About Wildfires Free Resources for Families Call for food, shelter, health services, and more. Help Me Grow Los Angeles 833.903.3972 Visit: www.HelpMeGrowLA.org |
በወረዳ 41 በሰደድ እሳት ቃጠሎ ለተጎዱ ነዋሪዎች ያሉ የእርዳታ ምንጮች 211 LA - Airbnb.org (ኤርቢኤንድቢ) የተባለው ድርጅት፣ ከ 211 LA ጋር በመተባበር በሰደድ አሳቱ ምክንያት በጊዜያዊነት ከቤታቸው የተፈናቀሉና ቤታቸውን እንዲለቁ ለተገደዱ ነዋሪዎች ጊዜያዊ የመኖሪያ ስፍራ ያለ ምንም ክፍያ አዘጋጅቷል። Recovery.lacounty.gov (የሎስ አንጀለስ አውራጃ) በሰደድ አሳቱ ለተጎዱ ነዋሪዎችም ሆነ የንግድ ተቋማት የመልሶ ግንባታ ሂደቱን ለመጀመር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የእርዳታ ምንጮችና የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ለመጠቀም እንደሚችሉ ያሳውቃል። ለመድን ድርጅቶች ዋስትናን ለመጠየቅና ማመልከቻዎችን ለማስገባት ዝግጅት አድርጉ፣ ቤታችሁን ከለቀቃችሁ ጀምሮ ያሉ የወጪ ደረሰኞችን በቅጡ ሰብስቡ፣ የመድን ኩባንያዎች የተለያየ ድንጋጌዎች ስለሚኖራቸው፣ በተቻለ ፍጥነት የየራሳችሁን መድን ድርጅት ወይንም ወኪላችሁን በማነጋገር፣ የመድን ሽፋናችሁ ምን ምን እንደሚያካትት፣ መጠኑም ምን ያህል እንደሆነ፣ ውስንነት ካለው ምን እንደሆነና፣ ማመልከቻችሁን በምታስገቡበት ወቅት ምን አይነት የሰነድ ማስረጃ እንደሚያስፈልግ አጣሩ። አብዛኛው የተከራዮች የመድን ሽፋን ተጨማሪ የኑሮ ወጪንም የሚሽፍን የመመሪያ ደንብ ያካተተ ነው። የመድን ሽፋናችሁን አስመልክቶ ከመድን ድርጅታችሁ ሰራተኞች ጋር የምታደርጉትን ንግግር፣ ቀን፣ ሰዓትና የወኪሉን/ወኪሏን ስም መዝግባችሁ አስቀምጡ። ግልጋሎት ለመስጠት የሚቀርቧችሁ የመድን ወኪሎች ወይንም ግምት ሰጪ ሰዎች ወቅታዊ የምስክር ወረቀት እንዳላቸው በ በይነ መረብ ላይ የ Department of Insurance (የመድን መስሪያ በት) ድረ-ገጽ በመሄድ ማጣራት ያስፈልጋል። አሁን ባለው ሕግ መሰረት፣ ግምት ሰጭ ግለሰቦች ወይንም ድርጅቶች አደጋው ከተከሰተ ከሰባት ቀን በፊት ግልጋሎት እንሰጣለን በሚል አገልግሎታችንን ተጠቀሙ ብሎ ለማግባባት ሊንቀሳቀሱ አይችሉም። የመድን ሽፋን ያለበትን ሰነድ ፣ አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ወረቀቶችና ንብረታችሁን በምስል ወይንም በተንቀሳቃሽ ምስል (ቪዲዮ) የንብረታቹን ዝርዝር በቀላሉ በዘመ ናዊ ስልኮቻችሁ በአጭር ጊዜ በመቅረጽ እንድትሰንዱ ያስፈልጋል። የ FEMA እርዳታ ለማግኘት ማመልከቻ አስገቡ ለመድን ድርጅታችሁ ማመልከቻ ሞልታችሁ ካስገባችሁ በሁዋላየመልሶ ግንባታ ተግባራችሁን በተቀላጠፈ መንገድ ለመጀመር ከ FEMA እርዳታ ለማግኘት ማመልከቻ አስገቡ፣ ማመልከቻውን ለማስገባት ሶስት ዘዴዎች አሉ በይነ መረብ ላይ - DisasterAssistance.gov በመሄድ ተንቀሳቃሽ ስልካችሁ ላይ የ FEMA App በመጎብነትና የ FEMA የእርዳታ መስመር ላይ 1-800-621-3362 በመደወል |
EVENTS
Thank you for your understanding.
PROGRAMS
Not yet a member? |